Thursday, June 20, 2013

ይድረስ ለእግር-ኳስ ፌዴሬሽናችን




                 ይድረስ ለእግር-ኳስ ፌዴሬሽናችን
እንደሚታወቀው በእግር ኳስ ፌዴሬሽናችን ቸልተኝነት ምክንያት የሚገባንን ነጥብ ተነጥቀናል ስለዚህ እስከመጨረሻው ድረስ
ተጠያቂነትንና ሀላፊነትን መውሰድ ያለበት እግር ኳስ ፌዴሬሽናች ነው::
ምክንያቱም የእግርክ ኳስ ፌዴሬሽን ባለስልጣናት ተገቢው  የእግር ኳስ ህግ እውቀት ሳይኖራቸው  በደመነፍስ የሚናገሩ እንዲሁም ወንበሩ ሳይገባቸው ስልጣን የተሰጣቸው መረጃ አያያዝ ላይ እንዲሁም ለሚዲያ  ይፋ በማድረግ በኩል ከፍተኛ ችግር ያለባቸው እንደ ፌዴሬሽን  ተቀናጅተው የማይሰሩ ከሀገር ጉዳይ ይልቅ ረብ የለሽ የግል ጉዳይ የሚያሳስባቸው
እንደው በጥቅሉ ስፖርት በሀገር ገጽታ ግንባታ በኩል ያለውን ፋይዳ ለይተው ያላወቁ፣ ስሜት የሌላቸው የሚከፈላቸውን ወፍራም ደሞዝ  አይተው  የተቀጠሩ መሆናቸውን ያሳያል
ይህን ሁሉ ልናገር የቻልኩ  ከአባይ ቀጥሎ የህዝቡን ስሜት በአንድነት ሲያስተሳስር ያያሁት ይህ የብሄራዊ ቡድናችን ድል ነበር!
ግን  በእንዚህ ግድ የለሽ የማይረቡ የፌዴሬሽን አካላት ምክንያት የደረሰብን “ውድቀት!!” ይቅር ሊባል የሚችል ነገር አይደለም
ስለዚህ ለሴንትራል አፍሪካ ጨዋታ ለተጨዋቾቻችን ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ በማድረግ እንዲሁም አሁን በተጨዋቾቻችን ላይ  የደረሰውን የስነልቦና  ችግር እንዲፈታ ማድረግ የግድ ይለዋል
በዚህም ምክንያት እንደኔ አስተያየት
ተጨዋቾቻችን የሚሰጣቸው የእረፍት ጊዜ ወደ አንድ ሳምንት ዝቅ እንዲል በማድረግ ከመደበኛ ደሞዛቸው በተጨማሪ ተገቢውን አበል እየከፈለ ሙሉ በሙሉ በትኩረት ዝግጅት እንዲያደርጉ እንዲሁም ልክ እንደ ፕሮፌሽናል(በርግጥ ፕሮፌሽናል ናቸው) ግን በቋንቋ(ረገጠው ለማለት መሬት እንዳይረግጡ) ፣ በእግር ኳስ ህጎች እና በሳይኮሎጂ የዳበረ እውቀት እንዲኖራቸው ማድረግ የፌዴሬሽኑ ግዴታ ነው ብየ ለማሳሰብ እወዳለሁ::



በዚህ ሀሳብ ከተስማሙ ሼር ያድርጉ !! የጎደለ ነገር ካለም አስተያየት ይስጡ


Saturday, June 15, 2013